Blog Archive

Monday 20 February 2017

ቢንያም መኮንን - የናዝሬቱ ኢየሱስ Binyam Mekonin - Yenazretu Iyesus (በድጋሚ የተስራ Remix) HD Video Feb. 2017




ፆም እኛን አንጂ እግዚአብሔርን አይለውጠውም!



ክርስቲያናዊ ፆም  መፀሃፍ ቅዱስ ምን ይላል?
ክርስቲያኖች እንዲጾሙ መፅሃፍ ቅዱስ ትእዛዝ አይሰጥም:: ነገር ግን መጸሃፍ ቅዱስ ጾምን ጥሩ: ትርፋማ እና ጠቃሚ እንደሆነ ይገልፅልናል:: በሃዋርያት ስራ መፅሃፍ ላይ እንደተፃፈው አማኞች ትልቅ ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ይጾሙ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 13:2; 14:23):: ብዙውን ግዜ ጾምና ፀሎት የተቆራኙ (የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ)ናቸው (ሉቃስ 2:37; 5:33):: ብዙውን ግዜ የጾም ትኩረት ምግብን ከመቀነስ ጋር ይያያዛል ነገር ግን የመጾም ዋና አላማ መሆን ያለበት ከዚህ አለም ትዕይንት አይንን አንስቶ ትኩረትን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ማድረግ ነው:: ጾም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ምን ያክል serious እንደሆነ የምንገልፅበት መንገድ ነው:: ጾም አዲስ ምልከታን እና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን ጥገኝነት እንድናደስ የረዳናል::

እንዲሁም ጾም በመፅሃፍ ቅዱስ በአብዛኛው ከምግብ ጋር የተያያዘ ይመስላል ነገር ግን ብዙ አይነት የጾም መንገዶች አሉ:: ለምሳሌ ትኩረታችንን ወደ እግዚአብሔር ለማድረግ የትኛውም ለጊዜው የምንተወው ወይም ከማድረግ የምንታቀበው ነገር እንደ መጾም ሊቆጠር ይችላል (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:1-6):: ጾም የሰዓት ገደብ ሊኖረው ይገባል በተለይ ከምግብ በምንጾም ግዜ:: ጾም ስጋችንን የምንቀጣበት ሳይሆን ትኩረታችንን ወደ እግዚአብሔር የምናዞርበት ውድ ግዜ ነው:: መፅሃፍ ቅዱሳዊ ጾም ጥቅሙ የሰውነት ክብደት ለመቀነስ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የጠለቀ ህብረት ለማድረግ ነው:: ማንም ሰው ሊጾም ይችላል ነገር ግን መጾም የማይችሉ አሉ ለምሳሌ ስኳር በሽተኞች... እንዲጾሙ አይገደዱም:: ማንም ስው የሆነን ነገር በጊዜያዊነት አሳልፎ ከእግዚአብሔር ጋር ለመቀራረብ በመስጠት መጾም ይችላል::

አይናችንን ከዚህች ዓለም ነገሮቿ ላይ ማንሳት መለማመድ ትኩረታችንን ወደ ክርስቶስ ለማዞር ስኬታማ መንገድ ነው:: ጾም እግዚአብሔርን እኛ የምንፈልገውን ነገር እንዲሰጠን የምናደርግበት መንገድ አይደለም:: መጾማችን እኛን እንጂ እግዚአብሔርን አይለውጠውም:: ጾም ከሌሎች ክርስቲያኖች ይልቅ መንፈሳዊ ሆነን የምንታይበት መንገድም አይደለም:: ጾም መጾም ያለበት ትህትና በተሞላበት እና በደስተኝነት(joyful) አኳኋን ነው:: መፅሃፍ ቅዱስ በማቴዎስ ወንጌል 6:16-18 ሲናገር "ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።" ይላል:: ጾማችን ልማድ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኘት ልምምድ የምናደርግበት ውድ ግዜ ይሁንልን:: እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካቹ::አሜን::

Wednesday 1 February 2017

Dawit Getachew - ተማርኪያለሁ (cover)
Original song by Dr. Dereje Kebede

አታገለኝ ትግል ከማልችለው ጋራ
አቅሜን አለማወቅ አጉል ስንጠራራ
ኤልሻዳይ ከሰማይ ወደታች እያየኝ
ትጥቄ ላልቶ ስወድቅ አዝኖ ሰበሰበኝ

አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረበዳ ኑሮው ይበቃኛል
እጆቼን ላንሳ ዛሬም ማርክርኸኛል
ተማርኪያለሁ

ወደ ምስራቅ ሲለኝ ምዕራቡን ስከተል
ያከለለልኝን ቅጥር ጥሼ ስዘል
ብዙ ተገጣጠብኩ ጠባሳ ብቻ ነኝ
ይቅርታው ብዙ ነው ምህረቱ ያስታመኝ

አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረበዳ ኑሮው ይበቃኛል
እጆቼን ላንሳ (ዛሬም ማርክርኸኛል
                   ተማርኪያለሁ) 2x

የዘላለም ቁጣ እንዳይሆን በእኔ ላይ
እግዚአብሔር በልጁ ቀደሰኝ ከሰማይ
በእግሮቹ ስር ሆኜ ትዕዛዙን ጠብቄ
መኖር ነው ምኞቴ በቀረው ዘመኔ

አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረበዳ ኑሮው ይበቃኛል
እጆቼን ላንሳ ዛሬም ማርክርኸኛል

                  ተማርኪያለሁ       (2x)

Daniel Amdemichael - የሰው እጅ የሌለበት

አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው
አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ
በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር
እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር
የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ
በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ

ፀጋው በእምነት ሆኖ አድኖኛል
እግዚአብሔር በልጁ ሕይወትን ሰጥቶኛል
ሁሉ ተፈጸመ በመስቀሉ
በሰላም እንድኖር በዘለዓለም ፍቅሩ

ላመስግነው በዝማሬ ይኼን ታላቅ ጌታ
ከጨለማ ለነጠቀኝ ከዚያ ክፉ ቦታ
ለወደደኝ ብርሃኑን ላበራ በሕይወቴ
መልካም ዜማ ለእርሱ ይሁን ይክበር መድሃኒቴ

አምላክ አበጃጀው ዘለዓለሜን
አንድ ልጁን ሰጥቶ ክርስቶስ ብቃቴን
የዘለላእም ህብረት ከአብ ጋራ
አገኘሁ ልጅነት በክርስቶስ ስራ

ምሥጋናውን ልዘምረው ልናገር ወንጌሉን
ጌታ ኢየሱስ እንደሚያድን ላብስር ምስራቹን
የአምላክ ፍቃድ ኢኼ ሆኗል ሰዎን የሚያመልጡበት
በልጁ ደም በእግዚአብሔር ጽድቅ አምነው ሚድኑበት

አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው
አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ
በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር
እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር
የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ
በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ

ምሥጋና ለአምላክ ፍቅር ለታደገኝ
እግዚአብሔር ከጨለማ መንገድ መለሰልኝ
ብርሃንን አሳየኝ ቅዱስ ቃሉ
ተፈጸመ እንዳለ ጌታ በመስቀሉ

ባመሰግን ይበዛል ወይ እኔስ በየእለቱ
ቅኔን ብቀኝ ባሸበሸብ ብዘምር በቤቱ
እልልስ ብል በታላቅ ድምጽ ብጮህ እስከደስታ
ባጨበጭብ በመስቀሉ ለዚህ ክቡር ጌታ

አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው
አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ
በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት
በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር
እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር
የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ
በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ

አሃ   (4x)


Download link:-  https://clyp.it/ntd454ki
Kalkidan Tilahun (Lily) U ቅጥር ሰርተህ


ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ

እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል   (2x)

እግዚአብሔር መሪ ነው ሁሌ ይመራኛል
ከረግረግ ከጭቃ እኔን ያወጣኛል
እግሬን በሰላሙ መንገድ የሚያቀና
የታመነ አምላክ ይድረሰው ምሥጋና

ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል         

እግዚአብሔር  መንፈስ ወደ እውነት መርቶኛል
በትዕዛዛትህ እንድሄድ አድርጐኛል
የቅዱሳንህን እግር የምትጠብቅ
በክንፎችህ ጥላ እኔን የምትደብቅ

ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል         

እርሱ የወደደው ተማምኖ ይኖራል
በትከሻው መሃል በክብርም ያድራል
እኔም ተወደድኩኝ ፍቅሩንም አየሁኝ
እግዚአብሔር ሳሳልኝ ተጠነቀቀልኝ

ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል  (4x)

Kalkidan Tilahun (Lily) U አመልካለሁ



አመልካለሁ እጆቼን አንስቼ
ጥያቄዬን ሁሉ ረስቼ
ዓላማዬ አንተ ብቻ  ነህ
ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ
ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ
ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ        (2x)

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ     (4x)

ሁልጊዜ ሥምህን እጠራለሁ እጠራለሁ
ኢየሱስ ኢየሱስ እልሃለሁ እልሃለሁ       (2x)
እልሃለሁ እልሃለሁ እልሃለሁ እልሃለሁ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ     (4x)


እንደ ማር ጣፈጠኝ ሥምህ አፌ ላይ
ከሥምህ የሚበልጥ (ሥም ይገኛል ወይ)   (2x)
ሥሞች ተሰብስበው ለሥምህ ሰገዱ
ከሥማቸው ይልቅ (ሥምህን ወደዱ)    (2x)

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ     (4x)

ምስጢሩ ምንድን ነው ምስጢሩ ይኼ ነው
ሥሙን ያስወደደው በሃሪው እኮ ነው     2x
ሥሙና ሕይወቱ አንድ ላይ ይሄዳል
እንደ ኢየሱስ ያለ ከወዴት ይገኛል    2x

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ     (4x)

እሺ ባይነትህ ታዛዥነትህ
ክብርህን ለመጣል ክብር መጣልህ   2x
ዝቅ ዝቅ ማለትህ ከፍ ከፍ አድርጐሃል
ከሥሞች የሚበልጥ ሥምን አሰጥቶሃል  2x

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ     (4x)


አመልካለሁ እጆቼን አንስቼ
ጥያቄዬን ሁሉ ረስቼ
ዓላማዬ አንተ ብቻ  ነህ
ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ
ዓላማዬ አንተ ብቻ ነህ
ከቶ አልሄድም ክበር ሳልልህ        

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ     (4x)


ምነው ነፍሴ እንደ ውኃ በሆንልኝ
አምላኬ ፊት እንደ ጅረት ቢፈስልኝ     (2x)