Dawit Getachew - ተማርኪያለሁ (cover)
Original song by Dr. Dereje Kebede
አታገለኝ ትግል ከማልችለው ጋራ
አቅሜን አለማወቅ አጉል ስንጠራራ
ኤልሻዳይ ከሰማይ ወደታች እያየኝ
ትጥቄ ላልቶ ስወድቅ አዝኖ ሰበሰበኝ
አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረበዳ ኑሮው ይበቃኛል 
እጆቼን ላንሳ ዛሬም ማርክርኸኛል 
ተማርኪያለሁ
ወደ ምስራቅ ሲለኝ ምዕራቡን ስከተል
ያከለለልኝን ቅጥር ጥሼ ስዘል
ብዙ ተገጣጠብኩ ጠባሳ ብቻ ነኝ
ይቅርታው ብዙ ነው ምህረቱ ያስታመኝ
አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረበዳ ኑሮው ይበቃኛል 
እጆቼን ላንሳ (ዛሬም ማርክርኸኛል 
                  
ተማርኪያለሁ) 2x
የዘላለም ቁጣ እንዳይሆን በእኔ ላይ 
እግዚአብሔር በልጁ ቀደሰኝ ከሰማይ
በእግሮቹ ስር ሆኜ ትዕዛዙን ጠብቄ
መኖር ነው ምኞቴ በቀረው ዘመኔ
አይኔን አንስቼ ጨፍኜ እንዳላይህ
በአጥንቴ ቀረሁ መነመንኩኝ ልጅህ
የምድረበዳ ኑሮው ይበቃኛል 
እጆቼን ላንሳ ዛሬም ማርክርኸኛል 
                 
ተማርኪያለሁ       (2x)

 
 
No comments:
Post a Comment