Blog Archive

Wednesday 1 February 2017

Kalkidan Tilahun (Lily) U ቅጥር ሰርተህ


ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ

እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል   (2x)

እግዚአብሔር መሪ ነው ሁሌ ይመራኛል
ከረግረግ ከጭቃ እኔን ያወጣኛል
እግሬን በሰላሙ መንገድ የሚያቀና
የታመነ አምላክ ይድረሰው ምሥጋና

ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል         

እግዚአብሔር  መንፈስ ወደ እውነት መርቶኛል
በትዕዛዛትህ እንድሄድ አድርጐኛል
የቅዱሳንህን እግር የምትጠብቅ
በክንፎችህ ጥላ እኔን የምትደብቅ

ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል         

እርሱ የወደደው ተማምኖ ይኖራል
በትከሻው መሃል በክብርም ያድራል
እኔም ተወደድኩኝ ፍቅሩንም አየሁኝ
እግዚአብሔር ሳሳልኝ ተጠነቀቀልኝ

ቅጥር ሰርተህ እኔን ከበህ
እንደ ዓይንህ ብሌን ተጠንቅቀህ
አቤት ጥበቃህ ጥበቃህ ያስደንቀኛል
ከክፉ ሁሉ ሁሉ አድነኸኛል  (4x)

No comments:

Post a Comment