Blog Archive

Tuesday 23 September 2014

Every single person has 24 hours in their day, 7 days in their week. We’ve all been given the same time, but it’s what we do with that time that makes our life. Oftentimes, people have so much going on that they aren’t able to get going forward. They stay stuck in busyness instead of making progress toward their goals and dreams.
The best way to get off of the treadmill, so to speak, and get moving forward again is to start the day by sowing a seed of time. When you sow a seed of time, when you invest that time by spending it with the Timeless One, you’ll find order in your days and have what you need to accomplish whatever it is that you need to accomplish.
Spending time with God doesn’t have to be boring and mundane. In fact, when you start experiencing His presence and sense Him speaking to your heart, it will become your favorite part of the day! We were created for fellowship and to fellowship with our heavenly Father.
The first step is to just be consistent. Growing with God is a process. Learning to hear Him is a process. You can’t speed the process up, but start by designating a place where you can be alone to pray and read your Bible every day.
I have a special chair in my house. I keep my Bible and a notebook there, and I keep a picture of my children there to look at as I pray for them. Sometimes I start my quiet time with a devotional book. Sometimes I sing or pray to get started. I don’t do it the same way every time. I’m more of a spontaneous person, and so my relationship with God reflects that. Now, Joel does the same thing, the same way every single day. (I fed him a tuna fish sandwich every day for the first 5 years of our marriage, and he was happy!) And that works for him. The point is to find what works for you! Just be yourself when you come to God.
Remember, God knows you, He created you, and He loves you just the way you are! But, He also loves you enough to help you grow. He wants you to get to know Him more. He wants you to be established and secure in His love for you. Make time for Him. Invest time with the Timeless One because it’s an investment that lasts throughout eternity!
“Then Christ will make his home in your hearts as you trust in him. Your roots will grow down into God's love and keep you strong.” (Ephesians 3:17, NLT)

Sunday 14 September 2014

የፍቅር ግንኙነት (from habeshastudent.com)

የፍቅር ግንኙነት

አንድ አባባል አለ፡፡ እንዲህ የሚል‹‹ ከሌሎች ውድቀት መማርን የመሰለ አሪፍ የማትረፊያ መንገድ የለም፡፡›› እንግዲህ የዚህ ጽሁፍም ዋና ዓላማው ከዚህ የወጣ ወይንም የዘለለ አይደለም፡፡ሴቶችንና የተቃራኒ ጾታ ግንኙነቶችን አስመልክቶ እጅግ ዋጋን ከከፈልኩ በኋላ የተማርኳቸውን እውነቶች በሚከተሉት አስር ነጥቦች እንደሚከተለው አቀርባቸዋለሁ፡፡

ምክር ቁጥር አንድ፡-
ወሲብ ያንን የሚወራለትን ያህል እንዳልሆነ አሁን በሚገባ ተረድቻ

ኮሌጅ ሳለሁ እኔው ራሴ ‹‹የፍቅር ሀንግኦቨር›› ብዬ ስም ያወጣሁለት ስሜት ሰለባ ነበርሁ፡፡ ምን መሰላችሁ፤ ከሴት ጋራ በወጣሁ ምሽት ማግስት ጠዋት ይሰማኝ የነበረውን የባዶነት ስሜት ማለቴ ነው፡፡ ስለዚህ ክስተት ቲቪውም ሆነ የምታዩአቸው ፊልሞች አይነግሩአችሁም፡፡ ይሁንና በጣም የሚያጋጥም ነገር ነው፡፡ የባዶነት ስሜት ብቻም ሳይሆን የጸጸት ስሜት ሳይቀር ይሰማል፡፡
ታዲያ ይህ የፍቅር ሀንግኦቨር ስሜት ለኔ በጣም ያልተለመደ ነገር ነበር፡፡ ምክንያቱም ኮሌጅ ሳለሁ ወሲብ ማለት ለኔ እንደ አምላኬ ያህል ስለነበር ነው፡፡ ጠዋት ቀን ምሽት ስለወሲብ እንጂ ስለሌላ አላስብም ነበር፡፡ ታዲያ ስታስቡት እንዲያ ያመለክሁት ወሲብ ለኔ ፍጹም ርካታን ባመጣልኝ ነበር፡፡ይሁንና እንደጠበቅሁት አላመጣልኝም፡፡
ታዲያ አንተንም እንዲህ ገጥሞህ ያውቅ ይሆን፤ የፍቅር ሀንግኦቨር ይዞህ ያውቃል? ይዞህ ከነበረ ቆም ብለህ ‹‹ ለምን እንዲህ ሆነብኝ፤ወሲብ ለእኔ እጅግ አስፈላጊ ከሆነ ለምን ባዶነትን አስከተለብኝ?›› ብለህ መጠየቅ አለብህ፡፡
እኔ ከዚህ የተነሳ ግራ የተጋባሁ ጊዜ የደረስኩበት ድምዳሜ ታዲያ ‹‹ ብዙ ሴክስ ብፈጽም ርካታው ይመጣል!›› የሚል ነበር፡፡ ግን ባዶነቱ ቀጠለ እንጂ አልጠፋም፡፡ በስተመጨረሻ ግን አንድ እውነት ገባኝ‹‹ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ለካስ የሚወራለትን ያህል አይደለም! ብዙ ተጋኖ ስለሚወራለት እነጂ የተባለውን ርካታ አያመጣም›› የሚል፡፡

ምክር ቁጥር ሁለት ፡-
አሁን ሴቶችን የሚያከብር ህይወት ለመኖር ወስኛለሁ፡፡

አንድ የገባኝ ሌላ ነገር ሴቶች ስለወሲብ ያላቸው አመለካከት ከወንዱ ፈጽሞ የተለየ መሆኑን ነው፡፡ ለምሳሌ አንዲት ሴት ለምን ከርሱ ጋር ወሲብ ፈጸምሽ ስትባል ‹‹ ስለምወደው እኮ ነው!›› ትላለች፤ ባታምንበትም እንኳ ማለት ነው፡፡ ይህ ለምን ሆነ ለምንል እንዲህ የሚል አባባል አለ፤‹‹ ሴቶች ፍቅርን ለማግኘት ወሲብን ይጠቀማሉ፤ ወንዶች ግን ወሲብን ለማግኘት ፍቅርን ይጠቀማሉ ! ››
ሴቷ ወሲብን ስትፈጽም የምታልመው አንድ ቀን ይህን ሰው አገባዋለሁ እያለች ሲሆን ወንዱ ግን ከመቼው ማድረግ የፈለገውን ሁሉ አድርጎ ለጓደኞቹ ሄዶ እስከሚያወራ ድረስ ነው የሚያልመው፡፡ ልክ እየሰራ እንዳልሆነ ህሊናው ያውቀዋል፤ ግን ማድረጉን ይቀጥላል፡፡ ለምን ቢባል ለሥጋዊ ርካታው ሲል! ሌላም ምክንያት ግን አለው፤ የወንድነት መገለጫም እንደሆነ ያስባል፡፡ ግን ሴትን ማታለል እንዴት ወንድነት ሊባል ይችላል!
አንድ አሁን የደረስኩበት እውነት ቢኖር ሴትን አከበርካት ማለት ራስህን አከበርክ ማለት ነው፡፡ ለምን አንድ ቀን ሁሉ ካለፈ በኋላ መጸጸት አይቀርም፡፡ ጸጸቱ ደግሞ ከደስታው ይልቅ ለረጅም ጊዜ አብሮን የሚቆይ ነው፡፡ ‹‹ሮብ ሮይ›› በተሰኘው ፊልም ላይ ዋናውን ገጸባህርይ የሚጫወተው ተዋናይ እንዲህ ሲል ይደመጣል ‹‹ አንድ ወንድ ለራሱ የሚሰጠው ስጦታ ቢኖር ከበሬታን ነው!›› ፡፡ በልብህ ልክ እንደሆነ የምታውቀውን ወይንም ለሴቷ ይጠቅማል የምትለውን በማድረግ ሴትን ካከበርካት ራስህን ማክበርህ እንደሆነ ልታውቅ ይገባል፡፡አብሮህ ከሚኖር ጸጸትም ለማምለጥህ ማረጋገጫ ይሆንሀል፡፡

ምክር ቁጥር ሶስት ፡-
ሴቲቱ የሌላ ሰው ሚስት እኮ ነች!

ለማለት የፈለግሁት ያኔ አብሬአቸው ስወጣ የነበሩ ሴቶች አብዛኞቹ ዛሬ የሌሎች ወንዶች ሚስቶች ሆነዋል፡፡ ታዲያ ዛሬ በነዚያ ወንዶች እግር ራሴን አኑሬ ሳስበው ምነው ባላደረግሁት ማለትም አብሬአቸው ባልወጣሁ ኖሮ ብዬ እቆጫለሁ፡፡ራሴን በራሴ ምታው ምታው ይለኛል፡፡ግን ምን ዋጋ አለው አንዴ ሆኖ አልፎአል!
በሌላ ጎኑ ሳየው ደግሞ እኔም ሳገባ ሚስቴ ከሌላ ሰው ጋር ትወጣ የነበረችና ያም ሰው የፈለገውን አድርጎባት እንደተለያት እያሰብኩ መኖሩን በጭራሽ አልፈልገውም፡፡ አንተስ ብትሆን ሚስትህ አንድ ወቅት ከሌላ ወንድ ጋር እንደነበረች ማሰብ የሚቀልህ ይመስልሐል? አያቸሁ በራስ ሲመጣ እንዴት ከባድ እንደሆነ!
ነገሩን ገፋ አድርገን ስናየው ደግሞ ሌላም ገጽታ አለው፡፡ ሴቲቱ የአንድ ወላጅ ልጅም እኮ ነች፡፡ የእኔ ሴት ልጅ ብትሆን ኖሮስ? እህቴስ ብትሆንስ? እንደእኔ ዓይነቱ ወንድ መጠቀሚያው አድርጎአት ቢተዋት እንደ ቀላል ነገር ሊቆጠር ይገባልን?
እንግዲህ ዛሬ ሴቶችን በሌላ ዓይን ማየት ጀምሬአለሁ፤ አንድ ሌላ ሰው የወደፊት ሚስት፣የሌላ ሰው ልጅ ወይንም እህት እንደሆኑ አድርገን ማሰብ እንድናከብራቸውና እንድንጠነቀቅላቸው ሊረዳን እንደሚችል ተምሬአለሁ፡፡

ምክር ቁጥር አራት ፡-
ወሲብ አሪፍ የተባሉትን ግንኙነቶቼን እንኳ ሳይቀር ገድሎብኛል፡፡

ኮሌጅ ሳለሁ አንዲት የልብ ወዳጅ ነበረችኝ፡፡የምኞቴን ዓይነት ሴት ነበር ያገኘሁት! ከርሷ ጋር የማሳልፋቸው ጊዜያት ሁሉ እጅግ ጣፋጮች ነበሩ፡፡ በቃ ተግባባን ነው የምላችሁ፡፡ ግን ታዲያ ጥቂት ቆየንና በእኔ አነሳሽነት ወሲብን መለማመድ ጀመርን፡፡
ብዙም ሳይቆይ የመገናኘታችን ምክንያቱ ወሲብ ብቻ መሆን ጀመረ፡፡እርሷን በይበልጥ ለመቀራረብና ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት ሁሉ ጠፋ፡፡ ታዲያ በመቀራረብ ፈንታ መራራቅ ጀመርን፡፡ ያን ድንቅ ህብረታችንን ወሲብ ገደለው!
ሰዎች ከሰዎች ጋራ በተለያዩ ደረጃዎች ማለትም በስሜት፣በአእምሮ፣በአካልና በመንፈስ ህብረትን ያደርጋሉ፡፡ ታዲያ እኔና ጓደኛዬ በአካል በሚሆነው ግንኙነታችን ላይ ብቻ ትኩረትን ስናደርግ ሌሎቹ የግንኙነት መስመሮቻችን ተቃጠሉብን፡፡ ያን ድርጊት ሳንለማመድ ታግሰን ብንቆይ ኖሮ ርግጠኛ ነኝ ዛሬም አብረን በሆንን ነበር፡፡
ይህ ሁኔታ እጅግ ብዙ ዎች ላይ ሲከሰት ታዝቤአለሁ፡፡ ይህ ለምን ይሆናል? ምክንያቱን ቀጥዬ አቀርበዋለሁ፡፡

ምክር ቁጥር አምስት ፡-
ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ሌሎችንም የግንኙነት መስመሮች ያበላሻል!

ከአንዲት ሴት ጋር ወሲብን በፈጸምኩ ጊዜ ሁሉ ሁለት ነገሮች እንደሚሆኑብኝ ታዝቤአለሁ፡፡እንዴት እንደሚከሰቱ አለማስተዋሌ እንጂ ያልተከሰቱባቸው ጊዜያት ነበሩ ለማለት አልደፍርም፡፡ያልኳችሁ ሁለቱ ነገሮች አንደኛው ለሴቲቱ ያለኝ ክብር መቀነሱ ( ባልፈልገውም እንኳ ማለቴ ነው) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሴቲቱ በእኔ እምነት ማጣቷ ነው(እርሷም ሳትፈልገው ማለት ነው)!
ይህ ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡መሆኑን ወይንም መከሰቱን ብቻ ነው የማውቀው፡፡ምናልባትም ስንፈጠር እንደዚያ ተደርገን ተሰርተን እንደሆነ ብዬም አስባለሁ፡፡ አንድ ነገር ግን ርግጠኛ ነኝ፤ የእኔ ብቻ ገጠመኝ አይደለም፡፡ በሌሎች ሰዎች ህይወትም ደግሞ ደግሞ ሲከሰት ዐይቻለሁኝ፡፡ብዙዎች ከፈጸሙት ቅድመ ጋብቻ ወሲብ የተነሳ የዛሬ ትዳራቸው ለብዙ ቀውስ እንደተዳረገ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ አለመተማመንንና አለመከባበርን ይዘው ነው ወደትዳር ህይወት የሚገቡት! እንግዲህ መተማመንና መከባበር ደግሞለአንድ ትዳር ህልውናና ጤንነት ወሳኝ ነገሮች እንደሆኑ ልብ ይሏል!
አንድ በቅርብ የተጋቡ ባልና ሚስትን አውቃለሁ፤ በወር ከአንድ ጊዜ ያነሰ የወሲብ ህብረት ነው ያላቸው፡፡ እርሱ አያከብራትም፤ይህን በደንብ ታውቃለች፡፡እርሷም አታምነውም፡፡ስለዚህ ራሷን ለርሱ መስጠትን በፍጹም አትፈልግም፡፡ ይህ አሳዛኝ ክስተት ቢሆንም ከምንገምተው በላይ አውነትና በጣምም የተለመደ ነው፡፡ይሁንና ማንም ስለዚህ ጉዳይ በአደባባይ በግልጽ አይናገርምም ሆነ አያስተምርም፡፡ቲቪ ላይ የምናያቸው ቕድመጋብቻ ፈጻሚ ጥንዶችም ስለዚህ ምንም የሚሉት ነገር የለም፡፡ በቃ ምን አለፋችሁ ሁሉ ሰው እንዳለ እያወቀ ሊናገረው የማይፈልገው እውነት ቢኖር ይሄ ነው፡፡

ምክር ቁጥር ስድስት፡-
እስከ ጋብቻ ታግሶ መቆየት በትዳር ውስጥ የተሳካና ጣፋጭ ወሲባዊ ህይወትን እንድንለማመድ ይረዳናል፡፡

ለምን ትሉ ይሆናል፡፡ መልሱ አጭርና ግልጽ ነው፡፡ እኔ ለርሷ ያለኝን አክብሮት እርሷም በእኔ ያላትን እምነት እንደጠበቅን ወደ ትዳር ስለምንገባ ነው፡፡ አንድ የተማርኩት ነገር ቢኖር ሴት ልጅ ወንዱን ካላመነችው መላው እኔነቷን ልትሰጠው አትፈልግም፤ከእርሱ ጋር መሆንም ደስታን አይሰጣትም፡፡
ውስጠ ምስጢሩ እንዲህ ነው፡፡ሴቶች ወሲብን ተጠቅመው ፍቅርን ለማግኘት ስለሚሞክሩና ወንዶችም በፍቅር አሳብበው ወሲብን ስለሚያገኙ ከዚህ የተሳሳተ መሠረት ላይ ቆመው ወሲብን ይፈጽማሉ፡፡ሴቲቱ ጓደኛዋን ላለማጣት ስትል ድርጊቱን መፈጸሟን ትቀጥላለች፡፡ወንዱም ከጓደኝነታቸው ይልቅ ወሲቡን ስለሚፈልገው ህብረታቸው ይቀጥልና ልክ ጋብቻው ተሳክቶ ከተፈጸመ በኋላ ሴቲቱም የምትፈልገው ሰው እጁዋ መግባቱን ስታረጋግጥ እርሱን ለማግኘት ስትል ትፈጽም የነበረውን ወሲብ ችላ ማለት ትጀምራለች፡፡እንዲያውም ከጋብቻ በፊት ወሲብ እናድርግ ብሎ እርሷን በመገፋፋቱ በልቧ ጥላቻና ቂምን መቋጠሯ ስለማይቀር ስለወሲብ ማሰብ እንኳ አትፈልግም፡፡ወንዱም ቢሆን ወሲብን ለራሱ ርካታ እንጂ ከርሷ ጋር ፍጹም አንድ ለመሆን ሲል ስለማያደርገው (ይህንን ስሜቱን እርሷ በደንብ ታውቅበታለች) የተበላሸ የወሲብ ህይወት መኖርን ይያያዙታል፡፡
ይህን ሁሉ ፈጥሬ የማወራችሁ አይምሰላችሁ፡፡አይደለም! ዛሬ ከኮሌጅ ህይወት ወጥቻለሁ፡፡ በዙሪያዬ ብዙዎች ሲያገቡ እያየሁ ነው፡፡ታዲያ ይህን ያልኩዋችሁን ሁሌም በብዙዎች ትዳር እየታዘብኩ አለሁ፡፡መፍትሔው ታዲያ ምንድነው ትሉ ይሆናል፤ መልሴ ‹‹ መጠበቅ፣ መጠበቅ አሁንም እስከጋብቻ ድረስ ታግሶ መጠበቅ!!!›› የሚል አጭርና ግልጽ መልስ ነው፡፡ ታግሶ የጠበቀ ወንድ ለሚስቱ ያለው ክብር ከፍተኛ ይሆናል፤ ሚስቲቱም እንዲሁ! ስለዚህ አንዳቸው ላንዳቸው ያላቸው ፍቅር ትኩስና ከፍተኛ ስለሚሆን የወሲብ ህይወታቸውም ጣፋጭና የተሳካ ይሆናል፡፡

ምክር ቁጥር ሰባት ፡-
ከሌሎች ሴቶች ጋራ ወሲብን አለመፈጸም ማለት በትዳር ውስጥ የተሳካና ጣፋጭ የወሲብ ህይወትን መኖር ማለት ነው፡፡

ወሲብ ምስጢራዊ ነገር ነው፡፡ አልፎ አልፎ የሚደረግ ነገር እንኳ ቢሆን በሰዎች ህይወት ውስጥ ጥልቅ የሆነ ውስጣዊ መተሳሰርን የሚፈጥር ነገር ነው፡፡ ታዲያ ችግሩ እዚህ ጋ ነው፤ ከሌሎች ሴቶች ጋር ብዙ ውስጣዊ መተሳሰርን ፈጥሬ ካለፍኩ ከወደፊቱዋ ሚስቴ ጋራ የጠበቀ መተሳሰር እንዳይኖረኝ እንቅፋትን ፈጥሮብኝ ያልፋል፡፡ልክ እንደ ስኮች ቴፕ ፕላስተር ማለት ነው፡፡ ስኮች ቴፕን ደጋግማችሁ የተጠቀማችሁበት ጊዜ የማጣበቅ ሐይሉ እያነሰ ሄዶ በስተመጨረሻ ከምንም ነገር ጋር መጣበቅ ያቅተዋል፡፡
ከጋብቻ በፊት ከሌሎች ሴቶች ጋራ መጣበቅ ከጀመርኩ ከወደፊቷ ሚስቴ ጋራ እንደሚገባኝ መጣበቅ ይሣነኛል፤በርሷም ሊኖረኝ የሚገባኝ ደስታ ይቀንሳል፤የሚገባትንም ፍቅር መስጠት እቸገራለሁ፡፡ ይሁንና ዛሬ ታማኝ ሆኜ የማሳልፋት እያንዳንዲቷ ቀን ለነገዋ ሚስቴ ተገቢ ፍቅርና አክብሮትን እድሰጣት የሚያስችለኝን ግኝኙነት እንድፈጥር ይረዳኛል፡፡
የሚገርም ነው! ማህበረሰባችን ምንዝርናን ማለትም በጋብቻ ውስጥ ያለ ዝሙትን አወግዛለሁ ይላል፡፡ በሌላ ጎን ግን ቅድመጋብቻ ወሲባዊ ግንኙነቶችን ሲኮንን አይታይም፡፡የጊዜን ስሌት ስናወጣው ቅድመጋብቻ ወሲብ እኮ ያው ምንዝርና ማለት ነው፡፡ ምንዝርና የትዳር ህብረትን ምን ያህል እንደሚጎዳ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ቅድመጋብቻ ወሲብ የሚያመጣው ቀውስ ግን ከዚህ ያልተናነሰ ነው፡፡በጋብቻ ውስጥ ሊኖር የሚገባውን መተሳሰርና መጣበቅ እጅጉን ይጎዳል!

ምክር ቁጥር ስምንት ፡-
ከአንዲት ሴት ጋራ በወሲብ መጣጣም አለመጣጣማችንን ለማወቅ የግድ አብረን መተኛት አያስፈልገንም!

ወሲብ ትዳርን ለማሟላት የተፈጠረልን ወይንም የተሠጠን ነገር እንጂ የትዳር የመጨረሻው ግብ አይደለም፡፡ እኔ የተማርኩት ነገር ይህንንም ነው፡፡ ልክ ኬክ ከተጋገረ በኋላ በስተመጨረሻ ለማሳመርና ለማጣፈጥ ብለን እንደምናለብሰው ዓይነት ክሬም ወሲብም ሌሎች የግንኙነታችን ክፍሎች ሁሉ በሚገባ የሚሰሩ ከሆነ ወሲብም ለትዳራችን ልዩ ማጣፈጫ ይሆነናል ማለት ነው፡፡ ሌሎች የግንኙነታችን ክፍሎች የሰመሩ ከሆኑ የወሲብ ህይወታችንም የተሳካ ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው ጥሩ የወሲብ ህይወት እንዳለኝ ለማወቅ ከወደፊቷ ሚስቴ ጋራ አብሬ በመተኛት መፈተሽ የሌለብኝ! በሌሎች የግንኙነት መስመሮች የተሳካልን ከሆንን በወሲብም ጉዳይ እንዲሁ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡
ሌላም ያስተዋልኩት አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ወሲብን የግንኙነቶቻችን መሰረትና መለኪያ አድርገን የምንወስደው ከሆነ የተሳካ የወሲብ ሕይወት እንዳይኖረን እንቅፋት ይሆናል፡፡እንግዲህ አስቡበት! የፈጸምነውን ወሲብ ለግንኙነታችን ጤናማነት መለኪያ እያደረግን ሁሌም በመነጽር የምንፈትሸው ከሆነ ወዳቂ መሆናችን የማይቀር ነው፡፡ ለምን ቢባል እንድንደሰትበት የተሰጠንን ነገር በገዛ እጃችን መታሰሪያችን ስለምናደርገው ነው፡፡
ይሁንና በሌሎች የግኝኙኘታችን መስመሮች ላይ ተግተን ከሰራንና ወሲብንም ዋና ጉዳይ ካላደረግነው ጣፋጭ የሆነ የወሲብ ህይወት እንዲኖረን የሚያስችለን መሥመር ውስጥ ገባን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የምንፈጽመውን ወሲብ ሁሌም አሪፍና አስደናቂ የማድረግ ግዴታ ውስጥ አንገባም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ሁሌም አስደናቂ መሆን አይችልምና!

ምክር ቁጥር ዘጠኝ ፡-
ከወሲብ ይልቅ እጅግ የሚያረካኝ ሌላ ነገር አግኝቻለሁ!

ይህን ስል ምን እያሰባችሁ እንደሆነ አውቄአለሁ፡፡ አውነቴን ነው አግኝቻለሁ፡፡ ‹ይህን› የሚበልጥ ነገር እንዳገኘው ወሲብ በተወሰነ ደረጃ ረድቶኛል ብል አልተሳሳትኩም፡፡ ያም ያገኘሁት ነገር እግዚአብሔር ነው፡፡
ግድ የላችሁም እንደምንም ጊዜ ሰጥታችሁ አስጨርሱኝ፡፡አጋነንክ ትሉኝ ይሆናል ግን አይደለም ስሜት የሚሰጥ ነገር ስለሆነ የምነግራችሁን እንደምንም ስሙኝ፡፡ እግዚአብሔር መጀመሪያውንም ሲሰራን ያለርሱ ሌላ ፍጹም ርካታን ሊሰጠን የሚኖር ነገር እንዳይኖር አድርጎ ነው የፈጠረን፡፡የሰውአፈጣጠር ሥርዓት ውስጥ ይህንን ጨምሮ ነው የሰራን፡፡ አንድ ሰው ጥሩ አድርጎ እንዳስቀመጠው ‹‹ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ እግዚአብሔር ብቻ ሊሞላው የሚችል የእግዚአብሔርን ቅርጽ የያዘ ባዶስፍራ አለ!››
ለዚህም ነው ሰዎች ሥራን፣ ጓደኞቻቸውን፣ ፋሽንንና ሌሎችንም ነገሮች ብንቀያይር እንኳ የመጨረሻውን ርካታ ማግኘት የሚሳነን፡፡ርካታ አልሰጥ ያሉንን እንተውና ደግሞ ወደሌሎች እንዞራለን፡፡ይሁንና ይህንኑ ርካታ ወደ ጌታ እስካልመጣን ድረስ ፈጽሞ አናገኘውም፡፡ ምክንያቱም እርሱ ብቻ ሊሰጠን የሚችለው ነገር ነውና!
እግዚአብሔር እጅግ ስለሚወደን በእርሱ እንጂ በሌላ እንድንረካ በፍጹም አይፈልግም፡፡ለእኛ ሁሌም እጅግ የተሻለውን ነገር ያውም እርሱን ይመኝልናል፡፡ምንም ይሁን ማንም ከእግዚአብሔር ይልቅ ጠቃሚ የሆነ የለም፡፡እኔ ራሴ የዚህ ነገር ምስክር ነኝ፡፡ ዕቃን በመግዛት፣በወሲብ ሽርሽሮች ብዛት ሊረካና ሊሞላ ያልቻለውን ህይወቴን ገብቶ ያሳረፈኝ እግዚአብሔር ነው፡፡ በግልጽ ለመናገር ኢየሱስን ወደ ህይወቴ እንዲገባ ስጋብዘው ኢየሱስ እንዲህ አለኝ‹‹ወደ እኔ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር አይራብም፣ በእኔ የሚያምንም አይጠማም፡፡(ዮሐ 6፤35)›› እነዚህ ቃሎች በህይወቴ እውን ሆኑ፡፡ከጌታ ጋር ህብረት ማድረግ የጀመርኩ ዕለት በውስጤ ያለውና በእግዚአብሔር ብቻ እንዲሞላ የተሠራው ክፍተቴ ተሞላና ፍጹም የሆነ ርካታን አገኘሁ፡፡ ባዶነት ፍጹም ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ እግዚአብሔርን ማወቄ ከወሲብ ይልቅ እጅግ ጥልቅ የሆነ ርካታን እንደሰጠኝ አየሁ፡፡

ምክር ቁጥር አሥር፡-
እስከ ጋብቻ ቀን ድረስ ታግሶ ለመቆየት የሚያስችል አቅምን እግዚአብሔር ሰጥቶኛል፡፡

አሁንማ ወሲብን ከፈጸምኩ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ግን ጭራሹኑ ወሲብን ሳልፈጽም እስከትዳሬ ቀን ድረስ ቆይቼ ቢሆን ኖሮ ምንኛ ደስ ባለኝ! ግን አልችልም! ምክንያቱም ዛሬ እምቆጭባቸው ብዙ ያለፉና ጥሩ ያልሆኑ ትዝታዎች አሉኝ፡፡ ቁጭቶቼ ያኔ በወሲብ ካገኘሁት ጊዜአዊ ደስታ ይልቅ ይኸው እስከዛሬ ድረስ ያናውዙኛል፡፡ ሴት እህቶቼን እንዴት እንደተጫወትኩባቸው ሳስብ አሁን ድረስ እቆጫለሁ፡፡ስለወደፊቱም ትዳሬ፣ ካገባሁ ማለቴ ነው፣የተሳካና የሚጸና ይሆንልኝ ይሆን ብዬም እጨነቃለሁ፡፡እግዚአብሔር አምላክ ግን ስላለፉት ድርጊቶቼም ሆነ ስለወደፊቱ ህይወቴ እንዳልጨነቅ እየረዳኝ ነው፡፡ እኔን በመለወጥ ሂደት ላይ ነው፣ እስካሁንም ብዙ ለውጦኛል፡፡
ያ ብቻም አይደለም፡፡ ወሲብን ለመፈጸም እስከትዳር ድረስ መቆየት የምችልበትንም አቅም እግዚአብሔር እየሠጠኝ እንዳለም አይቻለሁ፡፡ እውነት ነው አንዳንዴ ትግል አለብኝ ግን ትልቁ እግዚአብሔር እያሳለፈኝ እስካሁን አለሁ፡፡ በርሱ ዘንድ ሁሉ ይቻላል፡፡ እያንዳንዱ ቀን፣ሳምንትና ዓመት ባለፈ ቁጥር ታግሼ ከመጠበቄ የተነሳ ጥሩና የተሳካ ትዳር እንደሚኖረኝ አስባለሁ፡፡ በዚህ እንደ ወንድ ለህይወቴ እጅግ ወሳኝ በሆነ ጉዳይ ላይ እግዚአብሔርን በመታመኔ ከርሱ ጋራ ያለኝ ህብረት በጣም ጠንካራ ሆኖአል፡፡

ታዲያ የት እንጀምር?

እንደባልና እንደአባት ከሰዎች ጋራ ጥሩ ግንኙነቶችን መፍጠር ከፈለግህ መሥራት ልትጀምርበት የሚገባህ ጥሩ ስፍራ ቢኖር አንተው ራስህ ጋ ነው! ምስጢሩ ትክክለኛ ሚስት ለማግኘት ወይንም ትክክለኛ የሆኑ ልጆችን ለማፍራት ቆርጦ መነሳት አይደለም፡፡ ይልቁንም ቁልፉ ከራስህ መጀመር ነው፡፡ አንተን ጥሩ ባልና አባት ሊያደርግህ የሚችል በጣም ወሳኝ የሆነ ግንኙነት ቢኖር ከእግዚአብሔር ጋራ ያለው ግንኙነትህ ነው፡፡
እግዚአብሔር የወሲብ፣ የፍቅርና የግንኙነቶች ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡እንድንደሰትባቸው ብሎ የፈጠረልን ነገሮች ናቸው፡፡ስለአጠቃቀማቸው እርሱ ያወጣልንን ስርዓት ከተከተልን በሚገባ እንደሰትባቸዋለን፡፡አንድ የተረዳሁት ነገር ቢኖር እግዚአብሔር የሞራል አስከባሪ በመሆን ‹‹ይህን አድርግ፣ ይህን አታድርግ!›› እያለ አለቃ ወይንም መሪ መሆኑን ለማሳየት የሚሞክር አለመሆኑን ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ‹‹ከጋብቻ በፊት ወሲብን አትፈጽም! ›› ሲል ለራሴ ጥቅም ብሎ ነው፡፡ እርሱ ራሱ ስለሰራኝ ለእኔ የተሻለውንና የተሟላ ደስታ ሊሠጠኝ የሚችለውን ነገር ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

እግዚአብሔርን በግል እንዴት ማወቅ ይቻላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እየሱስ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ በሰው አምሳል ወደ ምድር በመምጣት የእግዚአብሔርን ማንነት በግልጽ ያሳየን የእግዚአብሔር ትክክለኛ አምሳያ ነው፡፡ ባጭሩ የእግዚአብሔርን ማንነት በግልጽ አሳይቶናል፡፡ ታዲያ እንዴት ነው ከርሱ ጋራ ህብረትን መፍጠር የምንችለው?
እግዚአብሔር ለእኛ እውነተኛ ፍቅር ስላለው እንድናውቀው ይፈልጋል፡፡ ይሁንና ይህ እንዳይሆን ግን አንድ እንቅፋት አለ፡፡ ይኸውም ኀጢአታችን ( ማለትም ሰውንና እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ መውደድ አለመቻላችን) በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል ጣልቃ በመግባት ህብረትን እንዳናደርግ እንቅፋትን ፈጥሮብናል፡፡
ስለሆነም እየሱስ የእኛን ሁሉ ሐጢአት በጫንቃው ላይ በመሸከም በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሞቶልናል፡፡ይህን ያደረገው እኛ ፍጹም ይቅር እንድንባልና በእግዚአብሔርም ተቀባይነትን እንዲኖረን ነው፡፡ በእኛ ፈንታ በመደብደብ በመዋረድ በመገረፍና በመሰቀል ታላቅን ዋጋ ከፍሎልናል፡፡ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተነስቶአል፡፡ስለዚህ ዛሬ ለዚህ ለከፈለልን ታላቅ መስዋዕት እርሱን ወደ ህይወታችን እንዲገባ በመጋበዝ ምላሽ እንድንሰጠው ይጠብቅብናል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ኖረው ካለፉ ወንዶች ሁሉ የላቀ ስብዕና የነበረው ወንድ ነበር፡፡ ሰዎች ግን ይህኛውን የማንነቱን ክፍል ብዙም ትኩረት አይሰጡትም፣ ግን በጣም እውነት የሆነ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ህይወትህ እንዲገባ ስትጋብዘው በምድር ላይ ከኖሩ ከማናቸውም ሰዎች ይልቅ ሰው መሆን ምን ማለት መሆኑን ጠንቕቆ የሚያውቀውን ሰው ነው እየጋበዝክ ያለኸው! ስለዚህ እውነተኛ ሰው እንድትሆን ይረዳሃል ፤ ይሁንና የሆሊውድ ፊልሞች የሚያሳዩንን ዓይነት ሰው ሳይሆን በህይወቱ ፍጹም የተሳካለትና ለሌሎችም ሕይወት ትርጉምን በመሥጠት በጣም ውድ የሆነ ህይወትን የሚኖር ዓይነት ሰው ያደርግሀል!
እውነተኛው ወንድ ምን ይመስል ይሆን ? እውነተኛ ወንድ እንደተኩላ ዓይነት ሰው አይደለም፤ የራሱ ፍላጎት መርካቱን ብቻ አያስብም፡፡ ይልቁንም እንደ እረኛ ለሌሎች ደህንነት የሚያስብ ዐይነት ባህርይ ያለው ሰው ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋራ ያለህ ህብረት ባደገ መጠን እውነተኛ ሰው ወይንም እውነተኛ ወንድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እየተረዳህ ትመጣለህ፡፡ ክርስቶስም ስለሴቶች ያለህን አስተሣሰብና ለእነርሱ የምታደርውን ክብካቤ ይለውጠዋል፡፡
ለዘለዓለም የሚዘልቅ ግንኙነትን ከክርስቶስ ጋራ መመስረት ትችላለህ፡፡ ‹‹ በርሱ ሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፡፡››ዮሐ 3፡16 እምነት ማለት መተማመን ማለት ነው፡፡ስላንተ በተከፈለው በክርስቶስ መስዋዕት ላይ ስትተማመን የዘላለም ህይወትን ታገኛለህ፤ይህም ማለት ከእግዚአብሔር ጋራ አሁን የሚጀምርና በህይወት ዘመንህ ሁሉ የምትቀጥለው ግንኙነት ማለት ነው፡፡ አሁን በልብህ እንዲህ ዓይነቱን ግንኙነት ለመጀመር ፍላጎቱ ካለህ ቀጥሎ የምታገኘውን ሀሳብ በሚመችህ መንገድ ለእግዚአብሔር ከልብህ በመናገር ግንኙነቱን መጀመር ትችላለህ፡፡
‹‹ ውድ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! በሐጢአቶቼ አንተን እንደበደልኩ አውቃለሁ፡፡ ኃጢአቶቼን ሁሉ ተሸክመህ በመስቀል ላይ ስለተሰቀልክልኝም አመሰግናለሁ፡፡ይቅርታህን ለመቀበል እፈልጋለሁ፡፡ካንተ ጋራ የጠበቀ ግንኙነትን መመስረት እፈልጋለሁ፡፡ ጌታዬና አዳኜ ሆነህ ወደሕይወቴ እንድትገባ እለምንሀለሁ፡፡ አንተ የምትፈልገውን ዓይነት ሰው እንድሆንልህ እባክህን እርዳኝ፡፡ አሜን!››
ተጨማሪ ምክርና ርዳታን ለማግኘትና በእግዚአብሔር ዕውቀት ለማደግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ማቴዎስ፣ ማርቆስ ፣ ሉቃስና ዮሓንስ የመሳሰሉትን ወንጌላት እንድታነብ አበረታታሀለሁ፡፡
ሰላም !
- See more at: http://www.habeshastudent.com/a/wolves.html#sthash.OL3rifKO.dpuf

Saturday 13 September 2014

3. ታቦት በዮሐንስ ራእይ

3. ታቦት በዮሐንስ ራእይ

pdf version
እንግዲህ በሁለቱ ኪዳኖች መካከል ያሉት መሠረታዊ ልዩነቶች ግልጽ ከሆኑልን፤ በመጀመሪያ ወደ ተነሳንበት የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ እንመለሳለን።

የዮሐንስ ራእይ
1119በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።

ይህ ክፍል በአንዳንዶች ላይ ጥያቄና ግራ መጋባት ሲፈጥር ይታያል። በአዲስ ኪዳን የታቦት አገልግሎት ሳይጠቀስ ቆይቶ ድንገት በራእይ መጽሐፍ ላይ የብሉይ ኪዳኑ ታቦት ሲጠቀስ ትንሽ ግር የሚላቸው ሰዎች አሉ።

በዚህ ክፍል የብሉይ ኪዳኑ ታቦት መጠቀሱ ለምንድነው? ክፍሉስ ሊያስተላልፍ የፈለገው መልዕክት ምንድነው? የክርስቶስ ተከታዮች እንደ ብሉይ ኪዳን አይነት ታቦት ሠርተው የብሉዩን ሥርዓት እንዲያካሂዱ ነው የሚያስተምረው ይህ ክፍል? አይደለም። የክርስቶስ ተከታዮች ወደ ብሉዩ ኪዳኑ ሥርዓት ይመለሱ ወይም የብሉዩንና የአዲሱን ሥርዓት ጎን ለጎን ያካሂዱ የሚል መልዕክት ነው በዚህ ክፍል ያለው? ይህን የሚያሳይ አንዳችም ነገር በዚህ ክፍል የለም። እንዲህማ ቢሆን አዲስ ኪዳንም ባላስፈለገ ነበር። ሁለቱን ኪዳኖች ጎን ለጎን በማካሄድ በሁለቱም በኩል ለመጽደቅ እንደማይቻልም ሁሉ ተመልክተናል፤ ስለዚህ ይህ ክፍል አዲስ ኪዳን ደጋግሞ ያስተማረውን ትምህርት የሚቃረን ወይም የሚገለብጥ ትምህርት ጨርሶ የለውም።

ታዲያ በዚህ ክፍል የታቦቱ መታየት ለምን አስፈለገ? ሊስተላለፍስ የተፈለገው መልዕክት ምንድነው? የዚህን ክፍል መልእክት ከመመልከታችን በፊት ስለ ዮሐንስ ራእይ አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮችን እንመልከት።

አንደኛ የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ የትንቢት መጽሐፍ ነው።

የዮሐንስ ራእይ 1
1 ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥ 2 እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ። 3 ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃልየሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።

ይህም ማለት እንደ ብሉይ ኪዳን የትንቢት መጽሐፍት ሁሉ ይህም የዮሐንስ ራእይ በአብዛኛው ወደፊት ሊመጣ ስላለውም ነገር የሚተነብይ መጽሐፍ ነው።

የዮሐንስ ራእይ 1
19 እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።

የዮሐንስ ራእይ እንግዲህ አሁን ስላለው ወይም ዮሐንስ በጻፈበት ጊዜ ስለነበረው ብቻ ሳይሆን ወደፊት ስለሚሆነውም የሚተነብይ መጽሐፍ ነው። እንዲያውም ከምዕራፍ 4 ጀምሮ ያለው ክፍል ወደፊት ሰለሚሆነው የሚተነብይ ስለወደፊት የሚናገር ትንቢት እንደሆነ በግልጽ ተጠቅሶአል።

የዮሐንስ ራእይ 4
1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ። ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።

ስለዚህ መነሻ የሆነን በምዕራፍ 11 የሚገኘው ጥቅስ የሚናገረው ወደፊት ስለሚሆን ትንቢት እንደሆነ በመጀመሪያ መረዳት ይገባናል።

ሌላው የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ብዙ ምሳሌያዊ ምልክቶችን (symbols) ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ማወቅ መጽሐፉን በሚገባ ለመረዳት ይጠቅመናል። ነገር ግን ምሳሌያዊ ምልክቶቹን ራሳችን እንደፈለግንና እንደመሰለን የምንተረጉመው ሳይሆን የምልክቶቹ ተርጓሚ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ መረዳት አለብን።

የዮሐንስ ራእይ የትንቢት መጽሐፍ እንደመሆኑ መጽሐፉን በይበልጥ ለመረዳት በመጽሐፍ ቅዱስ ስለተነገሩ ትንቢቶች መሠረታዊ መረዳት ሊኖረን ይገባል። በዚህ ጽሑፍ የተነሳንበትን ክፍል ለመረዳት የሚያስችለንን መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ብቻ በአጭሩ እንመለከታለን።

የዮሐንስ ራእይ የሚናገራቸው የወደፊት ትንቢቶች በአብዛኛዎቹ በብሉይ ኪዳን ዘመን በነበሩ ነብያትም የተተነበዩ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ዮሐንስ ራእይ ከምዕራፍ 6 እስከ ምዕራፍ 19 ያለው ክፍል በዳንኤል መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ላይ ስለተነገረው ሰባኛው ሱባዔ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ከመምጣቱ በፊት ስለሚሆነው ስለ መጨረሻው የሰባት ዓመት ታላቁ የመከራ ዘመን የሚናገር ነው። በተለይ ደግሞ ከሰባት ዓመቱ አጋማሽ ጀምሮ ማለትም በተቀሪዎቹ ሶስት ዓመት ተኩል ጊዜያት እጅግ ታላቅ መከራ በምድር ላይ እንደሚሆን ጌታም ታናግሮአል።

የማቴዎስ ወንጌል  24
21 በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።
22 እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።

በመከራው ዘመን ይሆናሉ ተብለው በብሉይም በአዲስም ከተተነበዩት ትንቢቶች አንዱ የእስራኤል ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ወደ አዲሱ ኪዳን መግባትን የሚናገር ትንቢት ነው።

ትንቢተ ሕዝቅኤል  20
33 እኔ ሕያው ነኝና በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ 34 ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ። 35 ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ። 36 በግብጽ ምድረ በዳ ከአባቶቻችሁ ጋር እንደ ተፋረድሁ እንዲሁ ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ 37 ከበትርም በታች አሳልፋችኋለሁ ወደ ቃል ኪዳንም እስራት አገባችኋለሁ 38 ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

በዚህ ክፍል ልክ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ምድር አውጥቶ በምድረበዳ ፊት ለፊት ከእነርሱ ጋር እንደ ተፋረደና ወደ ብሉዩ ቃል ኪዳን እንዳስገባቸው እንዲሁ እንደገና እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በምድረበዳ ፊት ለፊት እንደሚፋረድና ወደ አዲሱ ኪዳን እንደሚያስገባቸው የተነገረ ትንቢት ነው። "ወደ ቃል ኪዳንም እስራት አገባችኋለሁ" ቁጥር 37። እግዚአብሔር እንግዲህ እስራኤልን ወደ አዲሱ ኪዳን የሚያስገባቸው ልክ ወደ ብሉዩ ኪዳን እንዳስገባቸው አይነት በምድረበዳ ከሕዝቡ ጋር ፊት ለፊት በመፋረድ ነው። በሮሜ 11 ላይም የእስራኤል ሕዝብ የተላከላቸውን መሲሕ አሁን መቀበል እንዳልቻሉና በመንፈሳዊ እንቅልፍ ውስጥ እንዳሉ ነገር ግን ወደፊት ሕዝቡ ክርስቶስን እንደ መሲሕአቸው እንደሚቀበሉና እንደሚድኑ በስፋት ተብራርቶአል።

እንግዲህ በራእይ መጽሐፍ ወዳለው ወደ ተነሳንበት ጥቅስ ስንመለስ ይህንን የተነሳንበትን ጥቅስ በሚገባ ለመረዳት ጥቅሱ የሚገኝበትን ምዕራፍ 11 እና ምዕራፍ 12ን በሙሉ መመርመር ይገባል። በተለይ ከምዕራፍ 11፤15 ጀምሮ ማለትም ሰባተኛው መልአክ መለከት ከነፋ በኋላ እስከ ምዕራፍ 12 መጨረሻ ያለው የተያያዘ ሃሳብ ነው። በዚህም ክፍል ከታቦቱ ጋር ተያይዛ በቀጣዩ በምዕራፍ 12 የተጠቀሰች አንዲት ሴት አለች። ወደ ታቦቱ ከመምጣታችን በፊት ከታቦቱ ጋር ተያይዛ በተከታታይ ስለተጠቀሰችው ስለዚች ሴት በመጀመሪያ እንመልከት።

ይህች ሴት በምዕራፍ 11 የመጨረሻ ጥቅስ ከሆነው ከታቦቱ ጥቅስ ጋር አብራ ተያይዛ ከምዕራፍ 12 ቁጥር 1 ጀምሮ የተጠቀሰች ናት። እርሷም ከታቦቱ ጥቅስ ጋር ወዲያው ተከትላ የተገለጸች ሴት ስለሆነች የእርሷን ማንነት መረዳት ታቦቱ ለምን እዚህ ክፍል ላይ እንደተጠቀሰ እንድንረዳ ያግዘናል።

(የዮሐንስ ራእይ 11) 19በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ። (የዮሐንስ ራእይ  12) 1 ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። 2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች። 3 ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥ 4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ። 5 አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። 6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች። 7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥ 8 ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። 9ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።

በዚህ ክፍል ቁጥር 1 ላይ ስለ ሴቲቱ  መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር "ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ" ብሎ ይጀምርና የታየው ምልክት ምን እንደሆነ ሲገልጽ "ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች" ይላል። ስለዚህ ይህች ሴት ስለ አንድ ነገር የምታመለክት ምልክት (symbol) ናት ማለት ነው። መጽሐፍ ቁዱስ ራሱ ምልክት እንደሆነች ይናገራልና።

ሴቲቱ ወይም ሴትዮዋ ምንን እንደምታመለክት ወይም ትርጉሟ ምን እንደሆነ ለመረዳት የተገለጸችበትን ዓረፍተ ነገር እንመልከት። ሴቲቱ ፀሐይ እንደተጎናጸፈች፤ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች እንዳላትና በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የነበራት ሴት እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። ይህች ሴት እንግዲህ በፀሐይ በጨረቃና በአሥራ ሁለት ክዋክብት የምትመሰል ሴት ናት። ይህ ሴቲቱ የተገለጸችበት አገላለጽ ዘፍጥረት ላይ ዮሴፍ ካለመው ሕልም ጋር ተመሳሳይ ነው።

ኦሪት ዘፍጥረት
9 ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥እንዲህም አለ፦ እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብትምሲሰግዱልኝ አየሁ። 10 ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው አባቱም ገሠጸው፥ እንዲህም አለው፦ ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድር ነው? በውኑ እኔና እናትህ ወንድሞችህምመጥተን በምድር ላይ እንሰግድልህ ይሆን?

ይህ ክፍል ግልጽ እንደሚያደርገው ፀሐይና ጨረቃ አሥራ ሁለቱም ክዋክብት ሁሉ የእስራኤል ሕዝብ ምልክቶች ናቸው። አሥራ ሁለቱ ክዋክብት የእስራኤልን ሕዝብ አሥራ ሁለት ነገዶች ፀሐይና ጨረቃ ደግሞ የነገዶቹን አባትና እናት የሚያመለክቱ እንደሆነ በግልጽ ተቀምጦአል። ያዕቆብ የእስራኤል ሕዝብ አባት እንደሆነና "እስራኤል" የሚለው ስም ራሱ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ያወጣለት ስም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል (ዘፍጥረት  32፣27-28)። የአሥራ ሁለቱም የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች አባቶች ዮሴፍን ጨምሮ አሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንደሚተረጉመው ይህቺ ሴት እንግዲህ የእስራኤልን ሕዝብ የምታመለክት ናት።

ሌላው ስለዚህች ሴት በቁጥር 5 የተጠቀሰው ነገር አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ እንደ ወለደች እና ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ እንደተነጠቀ ነው። አሕዛብን በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውና ወደ እግዚአብሔር ዙፋን የተነጠቀው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ አያጠያይቅም። ክርስቶስም ከእስራኤል ሕዝብ ስለተወለደ ይህን ወንድ ልጅ የወለደችው ሴት የእስራኤልን ሕዝብ እንደሚያመለክት ሁለተኛው ማረጋገጫ ነው።

ወደ ሮሜ ሰዎች  9
4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤ 5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።

ሌላው ከሴትዮዋ ጋር አብሮ በራእይ 12፣7 ላይ የተጠቀሰው የእግዚአብሔር መልአክ ሚካኤል ስለ ሴትዮዋ ማንነት ሌላ ፍንጭ የሚሰጠን ነው። ምክንያቱም ሚካኤል የእስራኤል ሕዝብ መልአክ እንደሆነ በትንቢተ ዳንኤል ተጽፎአልና።

ትንቢተ ዳንኤል 12
1 በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።

እንግዲህ ከላይ ካየናቸው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መሠረት ካደረጉ ትርጉሞች እንደምንረዳው ከታቦቱ በመቀጠል ወዲያው የተጠቀሰችው ሴት የምታመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ እንደሆነ ግልጽ ነው።

ከላይ በሕዝቅኤል  20 ላይ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ወደ በረሃ አውጥቶ በዚያ እንደተፋረዳቸውና ወደ ብሉዩ ኪዳን እንዳስገባቸው እንዲሁ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ ከተበተኑበት አገሮች ከተሰበሰቡ በኋላ በምድረበዳ ፊት ለፊት እንደሚፋረዳቸውና ወደ አዲሱ ኪዳን እሥራት ውስጥ እንደሚያስገባቸው ተመልክተናል። እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብጽ እንዳወጣቸውና ከፈርዖን እንዳዳናቸው ሲናገር በዘጸአት ላይ እንዲህ ብሎ ነው የሚገልጸው።

ኦሪት ዘጸአት
194 በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።

በዚህም በራእይ ምዕራፍ 12 ላይ ተመሳሳይ ነገር ነው የምንመለከተው።

የዮሐንስ ራእይ  12
6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።
14 ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎችተሰጣት።

ሴቲቱ ከዘንዶው ማለትም በቁጥር 9 ላይ ማንነቱ እንደተገለጸው ከሰይጣን እንድታመልጥና "በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ" እንድትሸሸ "ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች" እንደተሰጣት እናነባለን። ይህም ልክ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከፈርዖን እጅ እንዳስጣላቸው እንዲሁ በታላቁ መከራ ዘመን እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ዘንዶው ከሚያስነሳባቸው ስደት እንደሚያስመልጣቸው የሚያመለክት ነው።

የሴቲቱ ሽሽትም ከሰባቱ ዓመት የመከራ ዘመን የመጨረሻውን አጋማሽ ማለትም ለሶስት ዓመት ተኩል እንደሆነም ተገልጾአል። ቁጥር 6 ላይ "ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን" ብሎ ሲጠራው ቁጥር 14 ላይ ደግሞ "ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ" ይለዋል። ማለትም አንድ አመት፥ ሁለት ዓመትና ግማሽ አመት ማለት ነው።

እንግዲህ በዚህ በሽሽት ዘመንና በበረሃ ነው እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ልክ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሁሉ ፊት ለፊት ተገልጦ ከተፋረደ በኋላ ወደ አዲሱ ኪዳን የሚያስገባቸው።

ምዕራፍ 12 ከመጀመሩ በፊት የታቦቱ መታየት እንግዲህ አሁን ይበልጥ ግልጽ ይሆንልናል። አንደኛ ቀድመን እንዳጠናነው ታቦት በእግዚአብሔርና በእስራእል ሕዝብ መካከል የተደረገው የብሉዩ ቃል ኪዳን ምስክር ነው። ይህ የቀድሞው ኪዳን ደግሞ ሌሎችን ሕዝቦች ሳይሆን እስራኤልን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንደሆነ ተመልክተናል። ይሄንንም የብሉዩን ኪዳን እስራኤል ባለመጠበቃቸውም ምክንያት አዲስ ኪዳን እንዳስፈለገም አይተናል። ስለዚህ በዮሐንስ ራእይ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝቡን ከመፋረዱ በፊት ማለትም ከምዕራፍ 12 በፊት እና በምዕራፍ 11 መጨረሻ የታቦቱ መታየት እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ የሚፋረድበትና ወደ አዲሱ ኪዳን የሚያስገባበት ጊዜ መድረሱን የሚያመለክት ነው። ምዕራፍ 12 ደግሞ የእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን የብሉዩን ኪዳን እንዳልጠበቁ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር በበረሃ ተፋርዶ በሕዝቅኤል እንደተተነበየው ወደ አዲሱ ኪዳን የሚይስገባበትን ቅድመ ሁኔታ የሚያሳይ ነው።

ቀደም ብለን እንዳየነው በመጽሐፍ ቅዱስ ታቦት ሲጠቀስ ያን በሲናና ተራራ የተፈጸመውን ቃል ኪዳን የሚያመለክት ነው። ይህም የቃል ኪዳኑ ተጋቢዎች የሆኑትን እግዚአብሔርንና የእስራኤል ሕዝብን እንዲሁም የቃል ኪዳኑ የውል ስምምነት የሆነውን ሕጉን እንደሚያስታውስ አይተናል።

በዚህ በራእይ ላይም ታቦት ያንን በሲና ተራራ የተደረገውን የብሉዩን ኪዳንና የስምምነቱ አካል የሆኑትን እግዚአብሔርን፣ የእስራኤልን ሕዝብና ሕጉን የሚያመለክት ነው። እንዲያውም ከታቦቱ ጋር አብረው በዚህ በራእይ የተጠቀሱት "መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ" ወዘተም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የብሉዩን ቃል ኪዳን ሲገባ በሲና ተራራ የሆነውን ሁኔታ የሚያስታውሱ ናቸው።

የዮሐንስ ራእይ
1119በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።

ኦሪት ዘጸአት  19
16 እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 17 ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸው ከተራራውም እግርጌ ቆሙ። 18 እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፥ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር
ስለዚህ እንደ ብሉይ ኪዳኑም ይህም ታቦት የተጠቀሰበት የራእይ ክፍል እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያለውን ጉዳይ የሚያሳይ፤ የእስራኤልን የወደፊት ዕጣ የሚመለከት ነገር ነው እንጂ የክርስቶስ ተከታዮች በአዲስ ኪዳን ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን የታቦት አገልግሎት እንዲጀምሩ የሚያስተምር አይደለም።

2. የብሉይና የአዲስ ኪዳን ልዩነት

2. የብሉይና የአዲስ ኪዳን ልዩነት

pdf version
ስለ ብሉይና ስለ አዲስ ኪዳን ንጽጽር ስናስብ ከሁሉ አስቀድሞ በመጀመሪያ አንድ ጥያቄ መመለስ ይገባናል። ይህም ከብሉዩ የተለየ አዲስ ሌላ ኪዳን ወይም አዲስ ውል ለምን አስፈለገ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ይኖርብናል። እግዚአብሔር ገና በብሉይ ኪዳን ዘመን ነው አዲስ ኪዳን እንደሚያስፈልግ በነብያቱ የተናገረው።

ትንቢተ ኤርምያስ 31
31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር 32 ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፦ 33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።

በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ራሱ ስለ አዲስ ኪዳን አስፈላጊነት በትንቢት በነቢዩ ኤርምያስ አማካኝነት ይናገራል። አዲስ ኪዳን ያስፈለገበትም ዋና ምክንያት የቀድሞውን ኪዳን እግዚአብሔር ስላልጠበቀ ወይም የቀድሞው ኪዳን መሠረት የሆነው ሕጉ መጦፎ ስለሆነ አይደለም። ነገር ግን ይህ ክፍል "እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና" እንደሚለው ዋናው ችግር ያለው ከቃል ኪዳን ተጋቢዎቹ አንዱ ወገን ማለትም የእስራኤል ሕዝብ የቃል ኪዳኑን ውል ማለትም ሕጉን ስላልጠበቁና መጠበቅም ስላልቻሉ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ በሮሜ መልዕክቱ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል።

ወደ ሮሜ ሰዎች  3
20 ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። 21 አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ 22 እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ 23ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ 24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ

ትልቁ የብሉይ ኪዳን ችግር እንግዲህ ሰው ሕግን ሁሉ ያለምንም ስህተት ማድረግና መፈጸም ባለመቻሉ ነው። ስለዚህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሊጸድቅ ስለማይችል በሕግ ላይ ያልተመሠረተ አዲስ ቃል ኪዳን አስፈለገ ማለት ነው። የአዲሱ ኪዳን መሠረት ለሰዎች ሁሉ ኃጢያት ስርየት በሞተው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን "ያለ ሕግ" የሚገኝ ጽድቅ ነው። ይሄም ጽድቅ ሰዎች በራሳቸው ጥረት ሕግን በመጠበቅ የሚያገኙት የሰው ጽድቅ ሳይሆን "እንዲያው በጸጋው" ከእግዚአብሔር የሚቀበሉት "የእግዚአብሔር ጽድቅ" ነው።

የብሉዩ ኪዳን ትልቁ ድክመት እንግዲህ ሰዎች ናቸው። በዚህም የተነሳ ብሉይ ኪዳን ሰዎችን የሚያጸድቅ ኪዳን መሆኑ ቀርቶ ሰዎች ሕግን መጠበቅ ባለመቻላቸው ምን ያህል ኃጢያተኞች እንደሆኑ ራሳቸውን የሚያዩበትና የሚኮንኑበት (condemn) ኪዳን ሆነ። የብሉዩ ኪዳን ለሰዎች ሕግንና በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፉ ትዕዛዛትን ቢሰጥም ሰዎቹ ያንን ሕግ የሚጠብቁበት ኃይል ግን አልሰጣቸውም ነበር። ለዚህ ነው ገና በብሉይ ኪዳን ዘመን ከላይ ባየነው የኤርምያስ ትንቢት እግዚአብሔር በአዲሱ ኪዳን ሕጉን በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰዎች ልብ ላይ ራሱ እንደሚጽፍ የሚናገረው።

„... ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ...“ ኤርምያስ 31፤33

በ2ኛ ቆሮንቶስ መልዕክት ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ የብሉይ ኪዳንን እና የአዲስ ኪዳንን አገልግሎት ሲያነጻጽር የብሉዩን "የኩነኔ አገልግሎት" ወይም "የሞት አገልግሎት" በማለት ሰዎች ኃጢያተኞች መሆናቸውን ከማሳየት በስተቀር ሊያጸድቃቸው የማይችል አገልግሎት መሆኑን ሲገልጽ በአንጻሩ ደግሞ ሰዎችን ሊያጸድቅ የሚችል በመሆኑ የአዲስ ኪዳንን አገልግሎት "የጽድቅ አገልግሎት" እያለ ይጠራዋል። በብሉዩ ኪዳን የእስራኤል ሕዝብ ሊፈጽመው የማይችሉትን በድንጋይ ላይ የተጻፈ ሕግን ተቀብለው እንፈጽማለንም ብለው ቃል ኪዳን አደረጉ ነገር ግን መፈጸም አልተቻላቸውም። አዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ራሱ ሕጉን በሰዎች ልብ ላይ የሚጽፍበት የተለየ ኪዳን ነው።

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች  3
3 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 4 በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን። 5 ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤ 6 እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 7 ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥ 8 የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም9 የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና። 10 ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና። 11 ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና

የአዲስ ኪዳን የኪዳኑ ውልና መሠረት ከብሉይ ኪዳን የተለየ ነው። የብሉይ ኪዳን ውል፤ እግዚአብሔር በሚሰጣቸው ምድር የእስራኤል ልጆች በሕጉ ያሉትን ትዕዛዛት ሁሉ ሊፈጽሙ፤ እግዚአብሔርም አምላክ ሊሆናቸና ሊባርካቸው፤ ባይፈጽሙ ግን እርግማን እንደሚመጣባቸው ከሰጣቸውም ምድር እንደሚያባርራቸው የሚገልጽ ውል ነው። የአዲስ ኪዳን ውል ደግሞ ከዚህ እጅግ የተለየ ነው። የውሉም መሠረት ሕጉ ሳይሆን ለዓለም ኃጢአት ሁሉ ደሙን ያፈሰሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰዎች በክርስቶስ ቢያምኑ እግዚአብሔር ኃጢያታቸውን ይቅር እንደሚላቸውና እንደሚያጸድቃቸው የሚገልጽ "ያለ ሕግ" የሆነ ውል ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች  3
21 አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ 22 እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ 23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ 24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ

የዮሐንስ ወንጌል 3
16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና

ወደ ሮሜ ሰዎች  7
4 እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ። 5 በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና፤ 6 አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም

አዲስ ኪዳን እንግዲህ ሰው በራሱ ሥራ እንደማይጸድቅና አዳኝ እንደሚያስፈልገው ተረድቶ በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋትነትና አዳኝነት አምኖ የሚድንበትና የሚጸድቅበት ዓለምን ሁሉ ሊያድን የሚችል ኪዳን ነው።

እዚህ ጋር ግን አንድ ልብ ማለት ያለብን ሁለቱን ኪዳኖች ጎን ለጎን በማካሄድ አንድም የሕግን ሥራ በመሥራት በራስ ለመጽደቅ መሞከር በሌላ ጎን ደግሞ በክርስቶስ ሥራ በጸጋ ለመጽደቅ መሞከር እንደማይቻል መገንዘብ ይገባናል። በአንድ በኩል በድንጋይ ጽላት ላይ ተጽፎ የተሰጠውን የሕግን ሥራ ሠርቶ ለመጽደቅ መሞከር፤ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲያው በጸጋ በክርስቶስ እምነት የሚገኘውን ጽድቅ ማግኘት አይቻልም። በገላትያ የነበሩ የክርስቶስ አማኞች በአንድ በኩል የሕግን ሥራ በመሥራት በሌላ በኩል ደግሞ በክርስቶስ በኩል በጸጋ ለመጽደቅ እንዳይጥሩ ትልቅ ማስጠንቂያ ተሰጥቶአቸው ነበር።

ወደ ገላትያ ሰዎች 5
2 እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። 3 ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ። 4 በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። 5 እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና። 6 በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።

ወደ ገላትያ ሰዎች  3
23 እምነትም ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር። 24 እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ 25 እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም። 26 በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤

የአዲስ ኪዳን ተከታዮች ከብሉይ ኪዳን ሕግ ነጻ ናቸው ማለት ግን ሕገወጥ ይሆናሉ የፈለጉትን ኃጢያት ይለማመዳሉ ማለት ግን አይደለም። በድንጋይ ላይ ከተጻፈ ከፊደል ሕግ ወጥተው ወደ መንፈስ ሕግ ይሸጋገራሉ ማለት ነው። ይህም በመንፈስ ቅዱስ እርዳታና ምሪት ከኃጢአት እየራቁ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በደስታ እያደረጉ መኖርን ያጠቃልላል። የአዲሱ ኪዳን የመንፈስ ሕግ ወይም በመንፈስ የመመላለስ ሕይወት ራሱን የቻለ ሰፊ ትምህርት ስለሆነ በዚህ ክፍል አንመለከተውም (በሮሜ 8 እና በገላትያ 5 ላይ ማጥናት ይቻላል)። ነገር ግን በአዲስ ኪዳን፤ ከብሉይ ኪዳን ሕግ መፈታት ማለት ሕገ ወጥ መሆን ወይም እንደፈለጉ ኃጢአትን ማድረግ እንዳልሆነ በዚህ ቦታ መጥቀስ ይገባል።

በመጨረሻም ሁለቱ ኪዳኖች እስራኤላዊ ካልሆኑ ሕዝቦች ጋር ያላቸውን ግንኙነቶች እንመልከት። ቃሉ እንደሚለው ሁለቱም ኪዳኖች የመጡት ለእስራኤል ነው። ሆኖም ቀደም ብለን እንዳየነው በብሉይ ኪዳን አንዳንድ ተሰድደው በእስራኤል ከሚኖሩ ምጻተኞች (ስደተኞች) በስተቀር ሌሎች ሕዝቦች የዚህ ኪዳን ተካፋዮች አልነበሩም። የኪዳኑ ውል የሆነው የሕጉ በረከቱም ሆነ መርገሙ ከአንድ ሕዝብ ማለት ከእስራኤልና ለእነርሱ ከተሰጣቸው ምድር ጋር የተቆራኘ ነው። እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ የሰጠውና ሌሎች ሕዝቦችን (አሕዛብን) የማያካትት (exclusive)፤ በሥጋ ከእስራኤል ዘር በመወለድ ብቻ የሚገባበት ኪዳን ነው።

አዲሱ ኪዳን ግን በትውልድ እስራኤላዊ ያልሆኑትን ሕዝቦች ሁሉ የሚያካትት (inclusive) ለዓለም ሁሉ መድኃኒትና መዳኛ መንገድ እንዲሆን የተሰጠና አህዛብንም አይሁድንም በክርስቶስ የሚያምኑትን ሁሉ እንደ አንድ ሕዝብ አድርጎ ያዋሃደ ኪዳን ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 3
16በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

ወደ ገላትያ ሰዎች  3
23 እምነትም ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር። 24 እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ 25 እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም። 26 በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤27 ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና። 28 አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና። 29 እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ

ወደ ኤፌሶን ሰዎች  2
11 ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤ 12 በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። 13 አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። 14-15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ 16 ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። 17 መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ 18 በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። 19 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም

የአዲስ ኪዳን መሠረትና የውል ስምምነት ከብሉዩ ኪዳን ጨርሶ የተለየ ነው። የአዲሱ ኪዳን የውል ስምምነት የተመሠረተው በድንጋይ ላይ የቀረጹትን ሕግጋት በመጠበቅ ወይም ባለመጠበቅ አይደለም። ነገር ግን በክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት በማመን ወይም ባለማመን ላይ ነው። እንደ ብሉይ ኪዳንም የእስራኤልን ሕዝብ ብቻ አቅፎ አሕዛብን የሚያገልል አይደለም፤ ነገር ግን ለእስራኤላውያንም ለአሕዛብም፤ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ መዳኛ እንዲሆን እግዚአብሔር የሰጠው ኪዳን ነው። በረከቱም በከነዓን ምድር ገብቶ ምድራዊ በረከትን መቀበል አይደለም፤ ነገር ግን የአዲስ ኪዳን ዋናው በረከት መንፈሳዊ ነው ይህም በእግዚአብሔር ፊት መጽደቅን፣ ከፍርድ መዳንን፣ የዘላለም ሕይወት ማግኘትን፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንን ወዘተ የመሳሰሉትን መንፈሳዊ በረከቶችን ያካተት ነው።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1
3 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።

የዮሐንስ ወንጌል 1
12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ 13 እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

የዮሐንስ ወንጌል 3
16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

የአዲስ ኪዳን መሠረትና የውል ስምምነት ከብሉዩ ኪዳን ጨርሶ የተለየ ስለሆነና ታቦቱ ደግሞ የብሉይ ኪዳኑ ውል የሆነውን የሕጉን የምስክር ጽላቶች የያዘ፤ ስለ ብሉይ ኪዳኑ የሚመሠከር፤ ከብሉይ ኪዳኑ ጋር የተቆራኘ ስለሆነ፤ ለአዲስ ኪዳን ምስክር ሊሆን አይችልም። እግዚአብሔር ያሰበውም የታቦት አገልግሎት እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በሲና ተራራ ስላደረው ቃል ኪዳን መመሥከር እንጂ በክርስቶስ ደም ስለሆነው ስለ አዲሱ ኪዳን እንዲመሠክር አይደለም።

አዲስ ኪዳን በድንጋይ ጽላት ሳይሆን በልብ ጽላት ላይ የሚጻፍ፣ ሰዎችን መኮነን ሳይሆን ማጽደቅ የሚችል ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝቡ ሁሉ የሆነ፣ በኮርማዎችና በከብቶች ደም ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሠረተ የተሻለ ኪዳን ነው።

የማርቆስ ወንጌል  14
22 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ሰጣቸውና። እንካችሁ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። 23 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፥ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ።24 እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።