ባልና ሚስት ቤት ቀይረው አዲስ ሰፈር ገብተዋል ።
በነጋታው ቁርስ እየበሉ ሚስት በመስኮቱ በኩል ልብስ እያጠበች ያለችን ጎርቤቷን እየት አድርጋ «ልብስ አስተጣጠብ አችልም እዴ? እየው ቆሻሻ ልብስ ታሰጣለች !» አለችው ለባሏ! ባሏ ቀና ብሎ መስኮቱን አንዴ እየት አደረገና ምንም ሳይናገር ወደ ቁርሱ ተመለሰ ። ይሄ ነገር ለብዙ ቀናት ተደጋገመ !! አንድ ቀን ጦዋት ሚስት «ኧረ ጎርቤቴ አለፈላት ዛሬ ንፁህ ልብስ አሰጣች ። ለመሆኑ በትክክል ማጠብ ማን ያስተማራት ይመስክሃል?› አለች በአድናቆት ባል ከቁርሱ ቀና ብሎ ሚስቱን አየት አደረገና «ትላንት ማታ መስኮቱን ወልውዬ አፅድቴዋለሁ » ብሎ መለሰላት ።

አለበለዚያ በእራሳችን ጉድፍ ሰዎችን ያለ እግባብ መውቀስ እንጀምራለን ።
የሉቃስ ወንጌል 6:42 | የማቴዎስ ወንጌል 7:5